image
image
image
image
image

የደንብ ጥሰት የፈጸሙ 262 በላይ ተቋማት እርምጃ ተወሰደባቸው።

ጥቅምት 28, 2018
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 28/2018 የአየር፡ የድምጽ የወንዝ ዳርቻ ብክለት ህግን የተላለፉ 262 በላይ ተቋማት እርምጃ እንደተወሰደባቸው የቦሌ ክ/ከተማ አከባቢ ጥበቃ አስታወቀ። የፅ/ቤቱ ሀላፊ አቶ አቶ አሜን ቅጣው እንደገለጹት ባለፈው 1ወር በክ/ከተማው የአካባቢ ፣ የድምፅና ፍሳሽ ብክለት እንዲሁም የአማቂ ጋዝ ልቀትን ለመቀነሰ የሚያስችሉ የቁጥጥር ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ በዚህም ባለፈው ወር ላይ በ435 ተቋማት በላይ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች መከናወኑን አንስተዋል፡፡ ተቋማቱ በአካባቢ ላይ የድምጽና የአየር ንብረት ብክለት :የወንዝ ዳርቻ ብክለት እንዳያስከትሉ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል መደረጉን የገለጹት ፅ/ቤት ሀላፊው ፤ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶአቸው ያላስተካከሉት ላይ እርምጃ መወሰዱንም ነው የተናገሩት። የደንብ ጥሰት በፈፀሙት ላይ 262 ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቅሰው በዚህም የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቛማት ፣ የምሸት ጭፈራ ቤቶች:መኖርያ ቤቶች እና ሌሎች ተቋማት እንደሚገኙበት ገልጸዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች